ኤርምያስ 51:42 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሕር በባቢሎን ላይ ይወጣል፤ ሞገዱም እየተመመ ይሸፍናታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሕሩ በባቢሎን ላይ ወጥቶባታል በሚናወጠውም ሞገዱ ተሸፍናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ጠላቶች እንደ ውቅያኖስ ማዕበል ወጥተው ከተማይቱን አጥለቀለቋት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕር በባቢሎን ላይ ወጣ፤ በሞገዱም ብዛት ተከደነች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሕር በባቢሎን ላይ ወጣ በሞገዱም ብዛት ተከደነች። |
በባሕሩ ዳር ባለው ምድረ በዳ ላይ የተነገረ ንግር፤ ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እየጠራረገ እንደሚመጣ፣ ወራሪ ከአሸባሪ ምድር፣ ከምድረ በዳ ይመጣል።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ጢሮስ ሆይ፤ እነሆ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ባሕር ሞገዷን እንደምታስነሣ፣ ብዙ ሕዝብ አስነሣብሻለሁ።
ከስድሳ ሁለቱ ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፤ ምንም አይቀረውም። የሚመጣው አለቃ ሰዎችም፣ ከተማውንና ቤተ መቅደሱን ይደመስሳሉ። ፍጻሜውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ ጥፋትም ታውጇል።