ኤርምያስ 50:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ቤዛቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ ለምድራቸው ዕረፍትን ለመስጠት፤ ተግቶ ይሟገትላቸዋል፤ በባቢሎን የሚኖሩትን ግን ዕረፍት ይነሣቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚዋጃቸው ብርቱ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ ነው፤ ምድሪቱንም ለማሳረፍ በባቢሎንም የሚኖሩትን ለማወክ ሙግታቸውን ፈጽሞ ይሟገታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ታዳጊያቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱ ራሱ ይረዳቸዋል፤ ሰላምን በምድር ላይ ያወርድላቸዋል፤ በባቢሎን ሕዝብ ላይ ገና መከራን ያመጣባቸዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቤዢአቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያሳርፍ ዘንድ፥ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ጠላቶቹን ወቀሳ ይወቅሳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተቤዢአቸው ብርቱ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፥ ምድርንም ያሳርፍ ዘንድ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ሙግታቸውን ፈጽሞ ይምዋገታል። |
“ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከግብጻውያን ቀንበር አወጣችኋለሁ። ለእነርሱ ባሪያ ከመሆን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድና በታላቅ ፍርድ እቤዣችኋለሁ።
የእስራኤል ቅዱስ፣ የሚቤዣችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ ሰራዊት እሰድዳለሁ፤ በሚመኩባቸውም መርከቦች፣ ባቢሎናውያንን ሁሉ እንደ ኰብላይ አመጣለሁ።
“የእስራኤል ንጉሥና ቤዛ እግዚአብሔር፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የፊተኛውም እኔ ነኝ፤ የኋለኛውም እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤ “ከተዋጊዎች ላይ ምርኮኞች በርግጥ ይወሰዳሉ፤ ከጨካኞችም ላይ ምርኮ ይበዘበዛል፤ ከአንቺ ጋራ የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፤ ልጆችሽንም እታደጋለሁ።
ሕዝቡን የሚታደግ አምላክሽ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ከእጅሽ፣ ያንገደገደሽን ጽዋ ወስጃለሁ፤ ያን ጽዋ፣ የቍጣዬን ዋንጫ፣ ዳግም አትጠጪውም፤
የያዕቆብ ዕድል ፈንታ የሆነው ግን እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነውና፤ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው። ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
በቀን እንድታበራ፣ ፀሓይን የመደበ፣ በሌሊት እንዲያበሩ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ያዘዛቸው፣ የሞገዱ ድምፅ እንዲተምም፣ ባሕሩን የሚያናውጥ፣ ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ እንዲህ ይላል፤
ፍቅርና ቸርነትን ለእልፍ አእላፍ ታሳያለህ፤ ይሁን እንጂ የአባቶችን በደል ከእነርሱ በኋላ በሚነሡ ልጆቻቸው ጕያ ትመልሳለህ፤ ስምህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ፣ ታላቅና ኀያል አምላክ ሆይ፤
የያዕቆብ ዕድል ፈንታ የሆነው ግን እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነውና፤ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው። ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
በሰራዊቱ ፊት፣ እግዚአብሔር ያንጐደጕዳል፤ የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቍጥር የለውም፤ ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁንስ ከከተማ ወጥተሽ፣ በሜዳ ላይ መስፈር አለብሽና፤ ወደ ባቢሎን ትሄጃለሽ፤ በዚያ ከጠላት እጅ ትድኛለሽ። እግዚአብሔር በዚያ፣ ከጠላቶችሽ ይታደግሻል።
እርሱን ስለ በደልሁ፣ እስኪቆምልኝ እስኪፈርድልኝም ድረስ፣ የእግዚአብሔርን ቍጣ እቀበላለሁ፤ እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤ እኔም ጽድቁን አያለሁ።
ስለዚህ መቅሠፍቶቿ በአንድ ቀን ይመጡባታል፤ ሞት፣ ሐዘንና ራብ ይሆኑባታል፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ስለ ሆነ፣ በእሳት ትቃጠላለች።