ኤርምያስ 48:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞዓብ ሕዝብ ሆይ፤ ሽብርና ጕድጓድ፣ ወጥመድም ይጠብቅሃል፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞዓብ የምትኖር ሆይ! ፍርሃትና ጉድጓድ ወጥመድም በአንተ ላይ አለ፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞአብ ሕዝብ ሆይ፥ “ሽብር፥ የሚያሰናክል ጒድጓድና ወጥመድ ይጠብቃችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሞአብ የምትኖር ሆይ! ፍርሀትና ጕድጓድ፥ ወጥመድም በአንተ ላይ አሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሞዓብ የምትኖር ሆይ፥ ፍርሃትና ጕድጓድ ወጥመድም በአንተ ላይ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ፣ ሽብር አመጣብሻለሁ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “እያንዳንዳችሁ ትሰደዳላችሁ፤ በሽሽት ላይ ያሉትንም የሚሰበስብ አይገኝም።