ኤርምያስ 48:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ! ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ! ሞዓብ የመሰደቢያ፣ በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ አለቀሱ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት ሰጠ! ስለዚህ ሞዓብ በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና መደንገጫ ሆኖአል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሞአብ ላይ ምን ዐይነት አስደንጋጭ ሁናቴ ደርሶ ነው የምታለቅሰው? እንዴትስ በዕፍረት ጀርባዋን ትሰጣለች? ስለዚህም ለጐረቤቶችዋ ሁሉ መሳለቂያና አስደንጋጭ ሆናለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዴት ተለወጠች! ከእፍረትም የተነሣ ሞአብ ጀርባዋን እንዴት መለሰች! ሞአብም በዙሪያዋ ላሉት ሁሉ መሳቂያና መሳለቂያ ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዴት ተገለበጠ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት መለሰ! ብላችሁ አልቅሱ። ሞዓብም በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና ድንጋጤ ይሆናል። |
በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ፣ እንዴት የተተወች ሆና ቀረች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው፣ እርሷ እንዴት እንደ መበለት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፣ አሁን ባሪያ ሆናለች።
ጌታ የጽዮንን ሴት ልጅ፣ በቍጣው ደመና እንዴት ጋረዳት! ከሰማይ ወደ ምድር፣ የእስራኤልን ክብር ወርውሮ ጣለው፤ በቍጣው ቀን፣ የእግሩን መቀመጫ አላስታወሰም።