ኤርምያስ 37:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም ንጉሡ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፤ “በግዞት ቤት ያሰራችሁኝ በአንተና በመኳንንትህ ወይም በዚህ ሕዝብ ላይ ምን ወንጀል ፈጽሜ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ደግሞ ንጉሡን ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “በእስር ቤት የጣላችሁኝ አንተን ወይስ ባርያዎችህን ወይስ ይህን ሕዝብ ምን በድያችሁ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ እንዲህ ብዬ ጠየቅሁት፦ “እስር ቤት ታስገባኝ ዘንድ በአንተ፥ በመኳንንትህና በዚህ ሕዝብ ላይ የፈጸምኩት ወንጀል ምንድነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ደግሞ ንጉሡን ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፥ “በግዞት ቤት የጣላችሁኝ አንተን፥ ወይስ አገልጋዮችህን፥ ወይስ ሕዝብህን ምን በድያችሁ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ደግሞ ንጉሡን ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ በግዞት ቤት የጣላችሁኝ አንተን ወይስ ባሪያዎችህን ወይስ ሕዝብህን ምን በድያችሁ ነው? |
“ታዲያ፣ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስም ሆነ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ገደሉትን? ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን ፈርቶ ምሕረት አልለመነምን? እግዚአብሔርስ በእነርሱ ላይ ለማምጣት ያሰበውን ቅጣት አልተወምን? በራሳችን ላይ እኮ ታላቅ ጥፋት እያመጣን ነው።”
ንጉሥ ሆይ፤ በፊቱ ቅን ሆኜ ስለ ተገኘሁ፣ በአንተም ፊት በደል ስላልተገኘብኝ፣ አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጐዱኝም።”
ጳውሎስም ወደ ሸንጎው ትኵር ብሎ በመመልከት፣ “ወንድሞች ሆይ፤ እኔ እስከዚች ቀን ድረስ በእግዚአብሔር ፊት በንጹሕ ኅሊና ተመላልሻለሁ” አለ።
ይሁን እንጂ ለሞት የሚያበቃ በደል ከተገኘብኝ፣ አልሙት አልልም፤ እነዚህ አይሁድ የሚያቀርቡብኝ ክስ እውነት ካልሆነ ግን፣ እኔን ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጥ የሚችል የለም፤ ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ!”