ኤርምያስ 37:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም በጕድጓድ ውስጥ እንዲቀመጥ ተደረገ፤ በዚያም ረዥም ጊዜ ቈየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም በጉድጓድ ውስጥ ለውኃ ማከማቻ ወደሚሆን ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፤ እርሱም በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ምድር ቤት ውስጥ በሚገኝ ክፍል ለብዙ ጊዜ ቈየሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ወደ ጕድጓድ ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፤ ኤርምያስም በዚያ ብዙ ቀን ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ወደ ጕድጓድ ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፥ ኤርምያስም በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፥ |
ስለዚህ ኤርምያስን ወስደው፣ በዘበኞች አደባባይ በነበረው በንጉሡ ልጅ በመልክያ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በገመድም ኤርምያስን ወደ ጕድጓዱ አወረዱት። ጕድጓዱም ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ዘልቆ ገባ።