ኤርምያስ 26:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የሰማችሁትን ይህን ሁሉ ቃል በጆሯችሁ እንድናገር እግዚአብሔር በርግጥ ስለ ላከኝ ብትገድሉኝ፣ የንጹሕ ሰው ደም በማፍሰሳችሁ እናንተ ራሳችሁንና ይህችን ከተማ፣ በውስጧም የሚኖረውን በደለኛ እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እነዚህን ቃላት ሁሉ በጆሮአችሁ እድናገር በእውነት ጌታ ወደ እናንተ ልኮኛልና፥ ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚህች ከተማ በሚኖሩባትም ላይ እንደምታመጡ በእርግጥ እወቁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ በጥንቃቄ ልታረጋግጡ ይገባል፤ ይኸውም እኔን ብትገድሉኝ፥ እናንተና የዚህ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ሁሉ ንጹሕ ሰው በመግደላችሁ በደለኞች ሆናችሁ ትገኛላችሁ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ እንድሰጣችሁ ወደ እናንተ የላከኝ በእርግጥ ራሱ እግዚአብሔር ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነቱ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚች ከተማ፥ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በርግጥ ዕወቁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነት እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚህች ከተማ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በእርግጥ እወቁ። |
ሮቤልም መልሶ፣ “በዚህ ልጅ ላይ፣ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
ንጉሥ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፤ በዚህ ፈንታ ልጁን ገደለው፤ በሚሞትበትም ጊዜ፣ “እግዚአብሔር ይየው፤ እርሱው ይበቀልህ” አለ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ከጨቋኙ እጅ አድኑት፤ መጻተኛውን፣ ወላጅ የሌለውንና መበለቲቱን አትበድሉ፤ አትግፏቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።
ኤርምያስም፣ ለባለሥልጣኖቹና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የሰማችሁትን ሁሉ በዚህ ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እንድናገር እግዚአብሔር ልኮኛል።
“ ‘ደም ምድሪቱን ስለሚያረክሳት፣ ደም ለፈሰሰባትም ምድር ስርየት ሊደረግላት የሚችለው በሌላ ሳይሆን በዚያው ደሙን ባፈሰሰው ሰው ደም ብቻ በመሆኑ፣ የምትኖሩባትን ምድር በደም አታርከሷት፤