ኤርምያስ 23:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ መንገዳቸው ድጥ ይሆናል፤ ወደ ጨለማ ይጣላሉ፤ ተፍገምግመውም ይወድቃሉ፤ በሚቀጡበትም ዓመት፣ መዓት አመጣባቸዋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች እንደ ምታዳልጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች፥ እነርሱም ወደ እርሷ ይገፈተራሉ ተፍገምግመውም ይወድቁባታል፤ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም መንገዳቸው የሚያዳልጥ መሬት ይሆናል፤ በጨለማም ሲራመዱ መንገዳቸውን ስተው ይወድቃሉ፤ በሚቀጡበትም ቀን ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ መንገዳቸው ድጥና ጨለማ ትሆንባቸዋለች፤ እነርሱም ፍግምግም ብለው ይወድቁባታል፤ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች እንደ ድጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች፥ እነርሱም ፍግምግም ብለው ይወድቁባታል፥ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። |
አሁን ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ተናገርሁት ስፍራ ምራው፤ መልአኬም በፊትህ ይሄዳል፤ ሆኖም የምቀጣበት ጊዜ ሲደርስ፣ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”
ጨለማን ሳያመጣ፣ በሚጨልሙትም ተራሮች ላይ፣ እግሮቻችሁ ሳይሰናከሉ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ። ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤ እርሱ ወደ ጨለማ ይለውጠዋል፤ ድቅድቅ ጨለማም ያደርገዋል።
“ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ፣ ጕድጓድ ውስጥ ይገባል፤ ከጕድጓዱም የሚወጣ፣ በወጥመድ ይያዛል፤ በሞዓብ ላይ፣ የቅጣቱን ዓመት አመጣለሁና፣” ይላል እግዚአብሔር።
ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም። ስለዚህ ከወደቁት ጋራ ይወድቃሉ፤ በሚቀጡ ጊዜ ይዋረዳሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
“አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እይ፤ ተመልከትም፤ በማን ላይ እንዲህ አድርገህ ታውቃለህ? በውኑ እናቶች ሕፃኖቻቸውን፣ ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ልጆች ይብሉን? ካህኑና ነቢዩስ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገደሉን?
ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜከላ፣ እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኵርንችት ነው፤ የጠባቂዎቻችሁ ቀን ደርሷል፤ የአምላክ የፍርድ ቀን መጥቷል፤ የሚሸበሩበትም ጊዜ አሁን ደርሷል።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤ “ከእንግዲህ ለጥቂት ጊዜ ብርሃን አለላችሁ፤ ጨለማ ሳይመጣባችሁ፣ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧል፤ የሚመጣባቸውም ፍርድ ፈጥኖባቸዋል።”