ኤርምያስ 22:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልትመለሱባት ወደምትናፍቋት ምድር ከቶ አትመለሱም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመመለስም ነፍሳቸው ወደምትመኛት ወደዚያች ምድር አይመለሱም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህችን አገር እንደገና ለማየት ትናፍቃለህ፤ ነገር ግን ዳግመኛ አትመለስባትም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሳችሁም ወደምትመኛት ወደዚያች ምድር አትመለሱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይመለሱባትም ዘንድ ነፍሳቸው ወደምትመኛት ወደዚያች ምድር አይመለሱም። |
ከእንግዲህ ስለማይመለስ፣ የተወለደባትንም ምድር ዳግመኛ ስለማያይ፣ ለተማረከው ንጉሥ አምርራችሁ አልቅሱ እንጂ፣ ቀድሞ ለሞተው አታልቅሱ፤ አትዘኑም።
በአባቱ ምትክ በይሁዳ ላይ ስለ ነገሠው፣ ከዚህ ስፍራ በምርኮ ስለ ተወሰደው፣ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “ከእንግዲህ አይመለስም፤
ይህ ኢኮንያን የተባለ ሰው፣ የተናቀና የተሰበረ ገንቦ፣ ማንም የማይፈልገው ዕቃ ነውን? እርሱና ልጆቹ ለምን ወደ ውጪ ተጣሉ? ወደማያውቁትስ ምድር ለምን ተወረወሩ?
የይሁዳንም ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ ሌሎች ከይሁዳ ወደ ባቢሎን ተማርከው የተወሰዱትንም ሁሉ ወደዚህ ስፍራ እመልሳለሁ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ የጫነባቸውን ቀንበር እሰብራለሁና።’ ”
የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ቍጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እንደ ፈሰሰ፣ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ በእናንተ ላይ ይፈስሳል፤ እናንተም የመረገሚያና የድንጋጤ፣ የመረገሚያና የመዘባበቻ ምልክት ትሆናላችሁ፤ ይህንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩም።’
ወደ ግብጽ የመጡት የይሁዳ ቅሬታዎች ወደ ይሁዳ ለመመለስ ቢመኙም ከጥቂት ስደተኞች በቀር አምልጦ ወይም ተርፎ ወደ ይሁዳ የሚመለስ አንድም ሰው አይኖርም።’ ”