ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ አሕዛብን፣ ‘እንዲህ ዐይነት ነገር በመካከላችሁ ተሰምቶ ያውቃል?’ ብላችሁ ጠይቁ። ድንግሊቱ እስራኤል፣ እጅግ ክፉ ነገር አድርጋለች።
ኤርምያስ 18:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሊባኖስ ተራራ ድንጋያማ ተረተር፣ በረዶ ተለይቶት ያውቃልን? ከጋራው የሚወርደውስ ቀዝቃዛ ውሃ፤ መፍሰሱን ያቋርጣልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ የሊባኖስ በረዶ የድጋያማውን ምድር ይተዋልን? ወይስ ከሩቅ የምትመጣው ቀዝቃዛይቱ ፈሳሽ ውኃ ትደርቃለችን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሊባኖስ ጭንጫማ ተራራዎች በበረዶ ያልተሸፈኑበት ጊዜ አለን? ከየተራራው ላይ የሚወርዱትስ ቀዝቃዛ ምንጮች ደርቀው ያውቃሉን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምንጭ ከዓለት ይጠፋልን? በረዶስ ከሊባኖስ ይጠፋልን? ወራጅ ውኃስ በኀይለኛ ነፋስ ይመለሳልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ የሊባኖስ በረዶ የምድረ በዳውን ድንጋይ ይተዋልን? ወይስ ከሩቅ የምትመጣው ቀዝቃዛይቱ ፈሳሽ ውኃ ትደርቃለችን? |
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ አሕዛብን፣ ‘እንዲህ ዐይነት ነገር በመካከላችሁ ተሰምቶ ያውቃል?’ ብላችሁ ጠይቁ። ድንግሊቱ እስራኤል፣ እጅግ ክፉ ነገር አድርጋለች።
ሕዝቤ ግን ረስቶኛል፤ ለማይረቡ ነገሮች ዐጥኗል፣ በራሱ መንገድ፣ በቀደሞው ጐዳና ተሰናክሏል፤ በሻካራው መሄጃ፣ ባልቀናውም ጥርጊያ መንገድ ሄዷል።