ኢሳይያስ 66:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊወለድ የተቃረበውን፣ እንዳይወለድ አደርጋለሁን?” ይላል እግዚአብሔር። “በሚገላገሉበት ጊዜስ፣ ማሕፀን እዘጋለሁን?” ይላል አምላክሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ወደ መውለድ የማደርስ እኔ እንዳይወለድ አደርጋለሁን? ይላል ጌታ፤ ሊወልድ የተቃረበውን ማኅፀንን እኔ እዘጋለሁን? ይላል አምላክሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲህ ይላል፦ “የመውለጃዋ ጊዜ እንዲደርስ ያደረግኋትን ሴት ልጅዋን እንዳትወልድ አደርጋለሁን? እንድትፀንስ ያደረግኋትን ሴት ማሕፀኗን እዘጋለሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ተስፋን ሰጠሁሽ፤ አንቺ ግን አላሰብሽኝም ይላል እግዚአብሔር። ሴት እንድትወልድ፥ መካንም እንዳትሆን የማደርግ እኔ አይደለሁምን?” ይላል አምላክሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ወደ መውለድ የማደርስ እኔ አላስወልድምን? ይላል እግዚአብሔር፥ የማስወልድስ ማኅፀንን እኔ እዘጋለሁን? ይላል አምላክሽ። |
እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፤ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የተግሣጽና የውርደት ቀን ነው፤ ልጆች ሊወለዱ ሲሉ ብርታት እንደሚታጣበት ቀን ሆኗል።
በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤ እርሱ ግን ጥበብ የሌለው ልጅ ነው፤ የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ፣ ከእናቱ ማሕፀን መውጣት የማይፈልግ ሕፃን ነው።