ኢሳይያስ 40:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል፤ “በምድረ በዳ የጌታን መንገድ፣ አዘጋጁ፤ ለአምላካችን አውራ ጐዳና፣ በበረሓ አስተካክሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ “የጌታን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሀ አስተካክሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ የሚል ድምፅ ይሰማል፦ “በምድረ በዳ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ! በበረሓም ለአምላካችን ጥርጊያ ጐዳና አብጁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዐዋጅ ነጋሪ ቃል በምድረ በዳ፥ “የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ፤ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሃ አስተካክሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሀ አስተካክሉ። |
እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤
“እነሆ፤ በፊቴ መንገድ የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ ደስ የምትሰኙበትም የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ ይመጣል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።