ሆሴዕ 9:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ሆይ፤ ደስ አይበልሽ፤ እንደ ሌሎችም ሕዝቦች ሐሤት አታድርጊ፤ በአምላክሽ ላይ አመንዝረሻልና፤ በየእህል ዐውድማውም ላይ፣ ለጋለሞታ የሚከፈለውን ዋጋ ወድደሻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤል ሆይ! ከአምላክህ ተለይተህ አመንዝረሃልና እንደ አሕዛብ ደስ አይበልህ፥ ሐሴትንም አታድርግ፤ በእህሉ አውድማ ሁሉ ላይ የዝሙትን ዋጋ ወድደሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በየዐውድማው የሚገኘውን የዝሙት ዋጋ ከበዓል የሚሰጥ በረከት መስሎአችሁ፥ ትወዱታላችሁ፤ ይህን በማድረጋችሁ ለአምላካችሁ ታማኞች ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ ስለዚህ እንደ ሌሎች ሕዝቦች መደሰታችሁንና ሐሴት ማድረጋችሁን ተዉ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ሆይ! ከአምላክህ ርቀህ አመንዝረሃልና እንደ አሕዛብ ደስ አይበልህ፤ ሐሴትንም አታድርግ፤ ከእህሉና ከወይኑ አውድማ ሁሉ ይልቅ የግልሙትና ዋጋን ወድደሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤል ሆይ፥ ከአምላክህ ተለይተህ አመንዝረሃልና እንደ አሕዛብ ደስ አይበልህ፥ ሐሴትንም አታድርግ፥ በእህሉ አውድማ ሁሉ ላይ የግልሙትናን ዋጋ ወድደሃል። |
ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤ ክሕደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤ እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣ እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣ ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ አስቢ፤ እስኪ አስተውዪ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰበርሁ፤ እስራትሽን በጣጠስሁ፤ አንቺም፣ ‘አላገለግልህም’ አልሽ፤ ከፍ ባለውም ኰረብታ ሁሉ ሥር፣ በእያንዳንዱም ለምለም ዛፍ ሥር፣ ለማመንዘር ተጋደምሽ።
እናደርጋለን ያልነውን ሁሉ እናደርጋለን፤ አባቶቻችን፣ ነገሥታታችንና ባለሥልጣኖቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች እንዳደረጉት ሁሉ እኛም ለሰማይዋ ንግሥት እናጥናለን፤ የመጠጥ ቍርባን እናፈስስላታለን። በዚያ ጊዜ የተትረፈረፈ ምግብ ነበረን፤ በመልካም ሁኔታ እንገኝ ነበር እንጂ ምንም ክፉ ነገር አልገጠመንም።
አንቺ በዖፅ ምድር የምትኖሪ፣ የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤ ነገር ግን ለአንቺም ደግሞ ጽዋው ይደርስሻል፤ ትሰክሪያለሽ፤ ዕርቃንሽንም ትጋለጫለሽ።
“ ‘ነገር ግን በውበትሽ ተመካሽ፤ ዝናሽንም ለአመንዝራነት ተጠቀምሽበት፤ ከዐላፊ አግዳሚው ጋራ ያለ ገደብ አመነዘርሽ፣ ውበትሽም ለማንም ሆነ።
“ ‘እናንተም፣ “ለዕንጨትና ለድንጋይ እንደሚሰግዱ እንደ አሕዛብ፣ በዓለምም እንደሚኖረው ሕዝብ ሁሉ እንሁን” አላችሁ፤ ነገር ግን በልባችሁ ያሰባችሁት ከቶ አይሆንላችሁም።
የተሳለው ሊገድል፣ የተወለወለውም እንደ መብረቅ ሊብረቀረቅ ነው! “ ‘ታዲያ፣ እንዴት ደስ ሊለን ይችላል? ሰይፉ የልጄን በትረ መንግሥት እንደ ማንኛውም በትር ንቋል።
በሰማርያ የሚኖረው ሕዝብ፣ በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ይፈራል፤ ሕዝቡም ያለቅስለታል፤ በክብሩ እጅግ ደስ ያላቸው ሁሉ፣ አመንዝራ ካህናትም እንደዚሁ ያለቅሱለታል፤ በምርኮ ከእነርሱ ተወስዷልና።
እርሾ ያለበትን እንጀራ የምስጋና መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤ የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን አሳውቁ፤ እናንተ የእስራኤል ልጆች የምትወድዱት ይህን ነውና፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፣ ዝማሬአችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፣ ጠጕራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ፤ ያን ጊዜ ለአንድያ ልጅ ሞት እንደሚለቀስበት፣ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።”