ሆሴዕ 5:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም፤ ዲቃሎች ወልደዋልና፤ ስለዚህ የወር መባቻ በዓላቸው፤ እነርሱንና ዕርሻቸውን ያጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና ጌታን አታልለዋል፤ አሁን ደግሞ እነርሱን ከርስታቸው ጋር የወሩ መባቻ ይበላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ራሳቸው ጣዖት አምላኪዎች ስለ ሆኑ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልተገኙም። ልጆቻቸውም እንደ ጣዖት ልጆች ተቆጥረዋል፤ ስለዚህ በዚህ ወር መባቻ እነርሱም ምድራቸውም አብረው ይጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ከድተዋል፤ አሁንም ኵብኵባ እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ወንጅለዋል፥ አሁንም አንድ ወር እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል። |
አልሰማህም ወይም አላወቅህም፤ ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤ አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና።
በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤ አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል።
“ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከተናገርሁት ቃል ከእንግዲህ የሚዘገይ የለም፤ የምለው ሁሉ ይፈጸማል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”
ወዮ ለእነርሱ፤ ከእኔ ርቀው ሄደዋልና! ጥፋት ይምጣባቸው! በእኔ ላይ ዐምፀዋልና። ልታደጋቸው ፈለግሁ፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።