La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 49:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ጋድን ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፤ እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጋድን ዘማቾች ይዘምቱበታል፥ እርሱ ግን ተከታትሎ ይዘምትባቸዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ጋድን ቀማኞች ያጠቁታል፤ እርሱም ዱካቸውን በመከተል መልሶ ያሳድዳቸዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ጋድን ሽፍ​ቶች ቀሙት፤ እር​ሱም ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ታ​ትሎ ቀማ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጋድም ዘማቾች ይዘምቱበታል እርሱ ግን ተከታትሎ ይዘምትባቸዋል

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 49:19
11 Referencias Cruzadas  

ልያም፣ “ምን ዐይነት መታደል ነው” አለች፤ ስሙንም ጋድ ብላ አወጣችለት።


የጋድ ልጆች፦ ጽፎን፣ ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤


“አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤ ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።


የእነዚህም አለቃ ዔጼር ነበረ፤ ሁለተኛው አዛዥ አብድዩ፣ ሦስተኛው ኤልያብ፣


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሓን መንፈስ ይኸውም የቴልጌልቴልፌልሶርን መንፈስ አነሣሥቶ የሮቤልን፣ የጋድንና፣ የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ እንዲወስድ አደረገ። እነዚህንም ወደ አላሔ፣ ወደ አቦር፣ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ ዳርቻ አፈለሳቸው፤ እነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።


ሌላው የምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ የሮቤል ነገድና የጋድ ነገድ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ እንደየድርሻቸው ከፋፍሎ በመደበላቸው መሠረት፣ ራሱ ሙሴ የሰጣቸውን ርስት ተቀበሉ።