ዘፍጥረት 47:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ከአባቶቼ ጋራ ሳንቀላፋ፣ ከግብጽ አውጥተህ እነርሱ በተቀበሩበት ቦታ ቅበረኝ።” ዮሴፍም፣ “ዕሺ፣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአባቶቼም ጋር በተኛሁ ጊዜ ከግብጽ ምድር አውጥተህ ትወስደኛለህ፥ በመቃብራቸውም ትቀብረኛለህ።” እርሱም፦ “እንደ ቃልህ አደርጋሁ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቶቼ በተቀበሩበት መቃብር መቀበር ስለምፈልግ በምሞትበት ጊዜ ከግብጽ አገር ወስደህ፥ እነርሱ በተቀበሩበት ስፍራ ቅበረኝ።” ዮሴፍም “እሺ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአባቶችም ጋር በአንቀላፋሁ ጊዜ ከግብፅ ምድር አውጥተህ ትወስደኛለህ፤ በአባቶችም መቃብር ትቀብረኛለህ።” እርሱም፥ “እንደ ቃልህ አደርጋለሁ” አለ። እርሱም፥ “ማልልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአባቶቼም ጋር በተኛሁ ጊዜ ከግብፅ ምድር አውጥተህ ትወስደኛለህ በመቃብራቸውም ትቅብረኛለህ። እርሱም፦ እንደ ቃልህ አደርጋለሁ አለ። |
በዚህ ሁኔታ፣ በመምሬ አጠገብ በመክፈላ ያለው የኤፍሮን ዕርሻ ቦታ ከነዋሻው በክልሉ ካሉት ዛፎች ሁሉ ጭምር ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈ፤
ከዚህም በኋላ አብርሃም በከነዓን ምድር፣ በመምሬ አጠገብ፣ መክፈላ በተባለች ዕርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ የሚስቱን የሣራን ሬሳ ቀበረ፤ ይህችም ኬብሮን ናት።
በገዛ ከተማዬ ሞቼ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ እቀበር ዘንድ፣ አገልጋይህን አሰናብተውና ይመለስ፤ ነገር ግን አገልጋይህ ከመዓም እነሆ፤ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋራ ይሻገር፤ ደስ ያለህንም ነገር አድርግለት።”
አሣሄልንም ከወደቀበት አንሥተው በቤተ ልሔም በአባቱ መቃብር ቀበሩት። ከዚያም ኢዮአብና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሡ ዐድረው፣ ሲነጋ ኬብሮን ደረሱ።
ተመልሰህ በመምጣት እንዳትበላና እንዳትጠጣ በነገረህ ቦታ እንጀራ በላህ፤ ውሃም ጠጣህ። ስለዚህ ሬሳህ በአባቶችህ መቃብር አይቀበርም’ ” ሲል ጮኾ ተናገረው።
ለንጉሡም፣ “ንጉሡን ደስ የሚያሠኘው ቢሆንና ባሪያህ በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፣ እንደ ገና እንድሠራት አባቶቼ ወደ ተቀበሩባት ወደ ይሁዳ ከተማ እንድሄድ ይፈቀድልኝ” አልሁት።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፤ ከአባቶችህ ጋራ ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋራ የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።