በዚህ ጊዜ ይሥሐቅ ክፉኛ እየተንቀጠቀጠ፣ “ታዲያ ቀደም ሲል ዐድኖ ያመጣልኝ ማን ነበር? አንተ ከመምጣትህ በፊት በልቼ መረቅሁት፤ እርሱም በርግጥ የተባረከ ይሆናል” አለው።
ዘፍጥረት 42:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ወንድሞቹን፣ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፣ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ወንድሞቹን፥ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፥ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ለወንድሞቹ “ገንዘቤ ተመልሶልኛል፤ ይኸው በስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት!” ብሎ ነገራቸው። ሁሉም በፍርሃት ተንቀጥቅጠው “እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለወንድሞቹም፥ “ብሬ ተመለሰችልኝ፤ እርስዋም በዓይበቴ አፍ እነኋት” አላቸው። ልባቸውም ደነገጠ፤ እየታወኩም እርስ በርሳቸው ተባባሉ፥ “እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ምንድን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለወንድሞቹም፦ ብሬ ተመለሰችልኝ እርስዋም በዓይበቱ አፍ እነኍት አላቸው። ልባቸውም ደነገጠ እየተንቀጠቀጡም እርስ በርሳቸው ተባባሉ፦ እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ምንድር ነው? |
በዚህ ጊዜ ይሥሐቅ ክፉኛ እየተንቀጠቀጠ፣ “ታዲያ ቀደም ሲል ዐድኖ ያመጣልኝ ማን ነበር? አንተ ከመምጣትህ በፊት በልቼ መረቅሁት፤ እርሱም በርግጥ የተባረከ ይሆናል” አለው።
አባታቸው ያዕቆብም፣ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጕድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።
የቤቱ አዛዥም፣ “አይዟችሁ አትፍሩ፤ በየስልቾቻችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ገንዘብ የሰጣችሁ የእናንተም የአባቶቻችሁም አምላክ ነው፤ እኔ እንደ ሆንሁ ብሩን ተቀብያለሁ” አላቸው። ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ አገናኛቸው።
እንዲሁም በገበታው ላይ የሚቀርበውን መብል፣ የሹማምቱን አቀማመጥ፣ የአስተናባሪዎቹን አቋቋምና የደንብ ልብሳቸውን፣ ጠጅ አሳላፊዎቹን፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያቀረባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ባየች ጊዜ እጅግ ተደነቀች።
ለውዴ ከፈትሁለት፤ ውዴ ግን አልነበረም፤ ሄዷል፤ በመሄዱም ልቤ ደነገጠ፤ ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፤ ነገር ግን አልመለሰልኝም።
እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፤ ከረዥም ጊዜ በፊት የተናገረውን፣ ቃሉን ፈጸመ፤ ያለ ርኅራኄ አፈረሰሽ፤ ጠላት በሥቃይሽ ላይ እንዲደሰት፣ የጠላትሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ።
“ ‘ከእናንተ በሕይወት የተረፉትን፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ድንጋጤ እሰድድባቸዋለሁ፤ ነፋስ የሚያንቀሳቅሰው የቅጠል ድምፅ ያስበረግጋቸዋል፤ የሚያሳድዳቸውም ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሮጣሉ፤ ይወድቃሉም።
በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። እዚያም እግዚአብሔር የሚጨነቅ አእምሮ፣ በናፍቆት የሚደክም ዐይንና ተስፋ የሚቈርጥ ልብ ይሰጥሃል።