ዘፍጥረት 36:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለቃ ቆሬ፣ አለቃ ጎቶምና አለቃ አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቆሬ አለቃ፥ ገዕታም አለቃ፥ አማሌቅ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ አለቆች እነዚህ ናቸው፥ እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቆሬ፥ ገዕታምና ዐማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም የኤልፋዝ ነገድ አለቆች ሲሆኑ፥ እነርሱም ዔሳው ከሚስቱ ከዓዳ የወለዳቸው ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቆሬ መስፍን፥ ጎቶን መስፍን፥ አማሌቅ መስፍን፤ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ እነዚህ የሓዳሶ ልጆች ናቸው ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኮሬ አለቃ ጎቶም አለቃ አማሌቅ አለቃ በኤዶም ምድር የኤልፋእ አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው። |
ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣
የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦ አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ።