ዘፍጥረት 35:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ከተመለሰ በኋላ፣ እግዚአብሔር ለያዕቆብ ዳግመኛ ተገለጠለት፤ ባረከውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከፓዳን-ኣሪም ከተመለስ በኋላ እንደገና ተገለጠለት፥ ባረከውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ዳግመኛ ተገለጠለትና ባረከው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከሁለት ወንዞች መካከል ከሶርያ ከተመለሰ በኋላ እንደገና በሎዛ ተገለጠለት፤ እግዚአብሔርም ባረከው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከሁለት ወንዞች መካከል ከሶርይ ከተመለስ በኍላ እንደ ገና ተገለጠለት ባረከውም። |
አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤
ይሥሐቅ ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር፤ ርብቃ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ የሚኖረው የሶርያዊው የባቱኤል ልጅ፣ የሶርያዊውም የላባ እኅት ነበረች።
እግዚአብሔርም ከጫፉ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፤ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ።
እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሥና ወደ ቤቴል ውጣ፤ እዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ” አለው።
እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፤ አድምጡኝ! አባታችን አብርሃም ወደ ካራን ከመምጣቱ በፊት፣ ገና በመስጴጦምያ ሳለ፣ የክብር አምላክ ተገልጦለት፣