ልጆቼን ብትበድላቸው ወይም ሌሎች ሚስቶች በላያቸው ላይ ብታገባ፣ ማንም ከእኛ ጋራ ባይኖርም እንኳ እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ምስክር መሆኑን አትርሳ።”
ዘፍጥረት 31:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ክምር ድንጋዩ እነሆ፤ በአንተና በእኔ መካከል ያቆምሁትም ሐውልት እነሆ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም ያዕቆብን አለው፥ “በእኔና በአንተ መካከል ይህ ክምር፥ ያቆምኩት ሐውልትም እነሆ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመካከላችን የቈለልኩት ድንጋይና ያቆምኩት ሐውልት እነሆ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም ያዕቆብን አለው፥ “እነሆ፥ ይህች የድንጋይ ክምርና ይህችም ሐውልት ምስክሮች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ያዕቆብን አለው፦ በእኔና በአንተ መካከል እነሆ ይህች ክምር እነሆም ያቆምኍት ሐውልት፤ |
ልጆቼን ብትበድላቸው ወይም ሌሎች ሚስቶች በላያቸው ላይ ብታገባ፣ ማንም ከእኛ ጋራ ባይኖርም እንኳ እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ምስክር መሆኑን አትርሳ።”
ይህን ክምር ድንጋይ ዐልፌ አንተን ለማጥቃት ላልመጣ፣ አንተም ይህን ክምር ድንጋይና ይህን ሐውልት ዐልፈህ እኔን ለማጥቃት ላትመጣ፣ ይህ ክምር ድንጋይ ምስክር ነው፤ ይህም ሐውልት ምስክር ነው።