ይሥሐቅ ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር፤ ርብቃ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ የሚኖረው የሶርያዊው የባቱኤል ልጅ፣ የሶርያዊውም የላባ እኅት ነበረች።
ዘፍጥረት 31:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመስጴጦምያ ካፈራው ሀብት ሁሉ ጋራ ከብቶቹን በሙሉ ወደ ፊት አስቀደመ፤ ወደ አባቱም ወደ ይሥሐቅ አገር፣ ወደ ከነዓን ምድር ጕዞውን ቀጠለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንጎቹንም ሁሉ፥ ያፈራውን ንብረት ሁሉ፥ ፓዳን-ኣራም ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመስጴጦምያ ሳለ ያገኛቸውን መንጋዎችና ዕቃዎችን ሁሉ ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንጎቹንም ሁሉ፥ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንጎቹንም ሁሉ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ በሁለት ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ። |
ይሥሐቅ ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር፤ ርብቃ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ የሚኖረው የሶርያዊው የባቱኤል ልጅ፣ የሶርያዊውም የላባ እኅት ነበረች።
አባቱ ያዕቆብን ስለ መረቀው፣ ዔሳው በያዕቆብ ላይ ቂም ያዘ፤ በልቡም፣ “ግድ የለም፤ የአባቴ መሞቻው ተቃርቧል፤ ከልቅሶው በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድላለሁ” ብሎ ዐሰበ።
የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ሊቀበልህ በመምጣት ላይ ነው፤ አራት መቶ ሰዎችም ዐብረውት አሉ” አሉት።