ዘፍጥረት 31:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሔልና ልያም እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “ከአባታችን ሀብት የምናገኘው ምን ውርስ አለ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሔልና ልያም መልሰው እንዲህ አሉት፥ “በአባታችን ቤት ለእኛ አንዳች ድርሻ ወይም ርስት አለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራሔልና ልያ ለያዕቆብ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “በአባታችን ቤት የውርስ ድርሻ ቀርቶልናልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሔልና ልያም መልሰው እንዲህ አሉት፥ “በአባታችን ቤት ለእኛ ድርሻ ወይም ርስት በውኑ አለን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሔልና ልያም መልሰው እንዲህ አሉት፦ በአባታችን ቤት ለእኛ ድርሻና ርስት በውኑ ቀርቶልናልን? |
የድንጋይ ሐውልት በማቆም ዘይት ቀብተህ የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ይህን አገር ፈጥነህ ልቀቅና ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመልሰህ ሂድ’ አለኝ።”
ከዚያም ሽማግሌዎቹና በከተማዪቱ በር አደባባይ የነበሩት ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “እኛ ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት፣ የእስራኤልን ቤት በአንድነት እንደ ሠሩ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፤ አንተም በኤፍራታ የበረታህ ሁን፤ ስምህም በቤተ ልሔም የተጠራ ይሁን።