ዘፍጥረት 30:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያ አሁንም ደግማ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም ደግማ ፀነሰች፥ ስድስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያ ዳግመኛ ፀነሰችና ለያዕቆብ ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም ደግማ ፀነስች፤ ስድስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም ደግማ ፀነሰች፥ ስድስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች |
እርሷም፣ “እግዚአብሔር በከበረ ስጦታ ዐድሎኛል፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት፣ ከእንግዲህ ባሌ አክብሮ ይይዘኛል”። አለች፤ ስሙንም ዛብሎን አለችው።
የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤ በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣ በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤