ያዕቆብም፣ “እንደምታዩት ጊዜው ገና ነው፤ መንጎቹ የሚገቡበት ሰዓት አይደለም፤ ታዲያ፣ ለምን በጎቹን አጠጥታችሁ ወደ ግጦሽ አትመልሷቸውም?” አላቸው።
ዘፍጥረት 29:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም፣ “ለመሆኑ ደኅና ነው?” አላቸው። እነርሱም፣ “አዎን ደኅና ነው፤ ልጁም ራሔል እነሆ፤ በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ናት” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ፦ “ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም፦ “አዎን ደኅና ነው፥ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ለመሆኑ እርሱ ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ፥ ደኅና ነው፤ እንዲያውም ልጁ ራሔል ያቺውልህ በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ነች” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እርሱ ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም፥ “አዎ ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል የአባቷን በጎች ይዛ ትመጣለች” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ፦ ደኅና ነው? አላቸው እነርሱም፦ አዎን ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች አሉት። |
ያዕቆብም፣ “እንደምታዩት ጊዜው ገና ነው፤ መንጎቹ የሚገቡበት ሰዓት አይደለም፤ ታዲያ፣ ለምን በጎቹን አጠጥታችሁ ወደ ግጦሽ አትመልሷቸውም?” አላቸው።
ያዕቆብም፣ “ሄደህ ወንድሞችህም፣ መንጎቹም ደኅና መሆናቸውን አይተህ ወሬያቸውን አምጣልኝ” አለው፤ ከኬብሮንም ሸለቆ ወደ ሴኬም ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣