ዘፍጥረት 27:45 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ቍጣው በርዶለት ያደረግህበትን ከረሳ በኋላ፣ እንድትመለስ እልክብህና ትመጣለህ። ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ለምን ልጣ?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድምህ ቁጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህበትንም እስኪረሳው ድረስ፥ ከዚያም ልኬ አስመጣሃለሁ፥ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊጣውም ሲበርድ ያደረግህበትን ነገር ይረሳል፤ ከዚያ በኋላ ሰው ልኬ አስመጣሃለሁ፤ ለምን ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ልጣ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያደረግህበትንም እስኪረሳው ድረስ፤ በአንድ ቀን ሁለታችሁን እንዳላጣ፥ ከዚያም ልኬ አመጣሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድምህ ቍጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህባትንም እስኪረሳው ድረስ ከዚይም ልኬ አስመጣሃለሁ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ? |
የደሴቲቱ ነዋሪዎች እባብ በእጁ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በርግጥ ነፍስ ገዳይ ነው፤ ከባሕር ቢያመልጥ እንኳ የፍርድ አምላክ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ተባባሉ።