ዘፍጥረት 24:55 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሟና እናቷም፣ “ልጅቷ ከእኛ ጋራ ቢያንስ ዐሥር ቀን ያህል ትቈይና ከዚያ በኋላ ልትሄድ ትችላለች።” ብለው መለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድምዋና እናትዋም፦ “ብላቴናይቱ አንድ ዐሥር ቀን ያህል እንኳ ከእኛ ዘንድ ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትሄዳለች” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የርብቃ ወንድምና እናትዋ “ልጅትዋ ዐሥር ቀን ያኽል ከእኛ ጋር ትቈይ፤ ከዚያ በኋላ ከአንተ ጋር ልትሄድ ትችላለች” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቷ እናቷና ወንድምዋ፦ “ብላቴናዪቱ ዐሥር ቀን ያህል እንኳ በእኛ ዘንድ ትቀመጥ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳለች” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድምዋና እናትዋም፦ ብላቴናይቱ አንድ አሥር ቀን ያህል እንኳ ከእኛ ዘንድ ትቀመጥ ከዚያም በኍላ ትሄዳለች አሉ። |
“ ‘ማንኛውም ሰው ቅጥር በተሠራለት ከተማ ውስጥ የሚገኝ መኖሪያ ቤቱን ቢሸጥ ከሸጠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አንድ ዓመት ሊዋጀው ይችላል፤ የመዋጀት መብቱ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ነው።
ከጥቂት ቀን በኋላም ሊያገባት ተመለሰ። የአንበሳውንም በድን ለማየት ከመንገድ ዘወር አለ፤ በበድኑም ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮ ተመለከተ፤ ማርም ነበረበት፤