ዘፍጥረት 24:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጅቷ ሮጣ ሄዳ፣ የሆነውን ሁሉ ለእናቷ ቤተ ሰቦች ነገረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብላቴናይቱም ሮጠች፥ ለእናትዋም ቤት ይህን ነገር ሁሉ ተናገረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጅትዋ ወደ ቤት ሮጣ ሄደችና የሆነውን ሁሉ ለእናትዋና ከእርስዋ ጋር ላሉት ሁሉ ነገረቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናዪቱም ሮጠች፥ ለእናቷም ቤት ይህን ሁሉ ነገር ተናገረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናይቱም ሮጠች ለእናትዋም ቤት ይህን ነገር ሁሉ ተናገርች |
ተደፍቼም ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ ለጌታዬ ወንድም የልጅ ልጅ የሆነችውን ቈንጆ፣ ለጌታዬ ልጅ እንዳገኝለት በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬ የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።
ላባም ወደ ያዕቆብ፣ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን እንዲሁም ወደ ሁለቱ ደንገጥሮቿ ድንኳኖች ገባ፤ ነገር ግን ምንም አላገኘም። ከልያ ድንኳን ከወጣ በኋላ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ።