ዘፍጥረት 23:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በኋላ አብርሃም በከነዓን ምድር፣ በመምሬ አጠገብ፣ መክፈላ በተባለች ዕርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ የሚስቱን የሣራን ሬሳ ቀበረ፤ ይህችም ኬብሮን ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኬብሮን በምትባል፥ ከመምሬ በስተ ምሥራቅ ማክፌላ፥ በከነዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው፥ ዋሻ ውስጥ አብርሃም ሚስቱን ሣራን ቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አብርሃም በከነዓን ምድር ባለችው በዚህችው ዋሻ የሚስቱን የሣራን አስከሬን ቀበረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ አብርሃም ኬብሮን በምትባል በመምሬ ፊት በከነዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ሚስቱን ሣራን ቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኍላ ኬብሮን በምትባል በመምሬ ፊት በከነዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ አብርሃም ሚስቱን ሣራን ቀበረ። |
ያዕቆብም፣ “ሄደህ ወንድሞችህም፣ መንጎቹም ደኅና መሆናቸውን አይተህ ወሬያቸውን አምጣልኝ” አለው፤ ከኬብሮንም ሸለቆ ወደ ሴኬም ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣
አስከሬኑን ወደ ከነዓን ምድር ወስደው አብርሃም ከኬጢያዊው ከኤፍሮን ላይ ከነዕርሻው በገዛው፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ በሚገኘው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።
ዳገት መውጣት ሲያርድ፣ መንገድም ሲያስፈራ፣ የአልሙን ዛፍ ሲያብብ፣ አንበጣም ራሱን ሲጐትት፣ ፍላጎት ሲጠፋ፤ በዚያም ጊዜ ሰው ወደ ዘላለማዊ ቤቱ ይሄዳል፤ አልቃሾችም በአደባባዮች ይዞራሉ።
አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሠኘበትና በአግባብ ካልተቀበረ፣ ከርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤