ዘፍጥረት 21:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሜሌክም፣ “እነዚህን ሰባት እንስት በጎች ለይተህ ለብቻ ያቆምሃቸው ለምንድን ነው?” ሲል አብርሃምን ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢሜሌክም አብርሃምን ለብቻቸው ያቆምሃቸው እነዚህ ሰባት ቄቦች በጎች ምንድን ናቸው? አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሜሌክም “እነዚህን ሰባት ሴት በጎች ለይተህ ያቆምካቸው ለምንድን ነው?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም አብርሃምን፥ “ለብቻቸው ያቆምሃቸው እነዚያ ሰባ ቄቦች በጎች ምንድን ናቸው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢሜሌክም አብረሃምን፦ ለብቻቸው ያቆምሃቸው እነዚህ ስባት ቄቦች በጎች ምንድር ናቸው? አለው። |
ዔሳውም፣ “ወደ እኔ ተነድቶ የመጣው ይህ ሁሉ መንጋ ምንድን ነው?” አለው። እርሱም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው።