ዘፍጥረት 21:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አብርሃም፣ የአቢሜሌክ አገልጋዮች ነጥቀው ስለያዙበት የውሃ ጕድጓድ መከፋቱን ለአቢሜሌክ ገለጠለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ባርያዎቹ በነጠቁት በውኃ ጉድጓድ ምክንያት አቢሜሌክን ወቀሰው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም፥ የአቤሜሌክ አገልጋዮች ስለ ወሰዱበት የውሃ ጒድጓድ ለአቢሜሌክ አቤቱታ አቀረበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም አቤሜሌክን ብላቴኖቹ በቀሙት በውኃ ጕድጓድ ምክንያት ወቀሰው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢሜሌክንም ባሪያዎቹ በነጠቁት በውኃ ጕድጓድ ምክንያት አብርሃም ወቀሰው። |
እርሷም፣ “እባክህ፤ ባርከኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።