ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ሜንጦዎችንና ከእነዚሁም ጋራ የተያያዙ ዕቃዎች። ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር።
ዘፀአት 38:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕቃዎቹንም ሁሉ ይኸውም ምንቸቶቹን፣ መጫሪያዎቹን፣ መርጫ ጐድጓዳ ሳሕኖቹን፣ ሜንጦዎቹንና የእሳት መያዣዎቹን ከንሓስ ሠሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ፥ ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖቹን፥ ሜንጦቹን፥ ማንደጃዎቹን ሠራ፤ ዕቃዎቹን በሙሉ ከነሐስ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመሠዊያው ላይ ያሉትንም የመገልገያ ዕቃዎች፥ ድስቶችንም፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም፥ ጐድጓዳ ሳሕኖችንም፥ ሜንጦዎቹንም፥ ማንደጃዎቹንም ከነሐስ ሠራ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦዎቹንም፥ የእሳት ማንደጃዎቹንም አደረገ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦቹንም፥ ማንደጃዎቹንም አደረገ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አደረገ። |
ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ሜንጦዎችንና ከእነዚሁም ጋራ የተያያዙ ዕቃዎች። ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር።
እንዲሁም ስፋቱ ከጠርዝ እስከ ጠርዝ ዐሥር ክንድ፣ ቁመቱ ዐምስት ክንድ የሆነ ክብ ገንዳ ከቀለጠ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ ሆነ።
በዚያ ጊዜ ካህናቱ ከሕዝቡ ጋራ ባላቸው ግንኙነት የሚፈጽሙት ወግ ነበር፤ ይኸውም ማንም ሰው መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለውን ሜንጦ ይዞ ይመጣል፤