ዘፀአት 2:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕፃኑም እኅት የሚደርስበትን ነገር ለማወቅ ራቅ ብላ ቆማ ታይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኅቱም ምን እንደሚደርስበት ለማየት በሩቅ ቆማ ትከታተለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕፃኑም እኅት የሚደርስበትን ነገር ለማየት ራቅ ብላ ትጠባበቀው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኅቱም ምን እንደሚደርስበት ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትጐበኘው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኅቱም የሚደርስበትን ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትመለከት ነበር። |
የእንበረም ሚስቱ ዮካብድ ትባል ነበር፤ እርሷም በግብጽ አገር ከሌዋውያን የተወለደች የሌዊ ዘር ነበረች። ከእንበረምም አሮንን፣ ሙሴንና እኅታቸውን ማርያምን ወለደች።