ዘዳግም 32:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንስር ጐጆዋን በትና፣ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፣ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ፣ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንስር ጎጆዋን ቆስቁሳ፥ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ይወስደዋል፥ በክንፎቹም ያዝለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጫጩቶችዋ ላይ እንደምታንዣብብ፥ ጎጆዋን እንደምትጠብቅ ንስር፥ እርሱን ለመያዝ ክንፎቹን ይዘረጋል፤ በክንፎቹም ጫፍ ይደግፈዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንስር ጫጩቶቹን በክንፎቹ በታች እንደሚሰበስብ፥ በጎኑም እንደሚያቅፍ፥ በክንፎቹ አዘላቸው፤ በደረቱም ተሸከማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ 2 በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ 2 ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ 2 በክንፎቹም አዘላቸው። |
በዐናት ላይ እንደሚያንዣብቡ ወፎች፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲሁ ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤ በላይዋ ያልፋል፤ ያድናታልም።”
መቀነት በሰው ወገብ ላይ እንደሚታሰር፣ መላው የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋራ ተጣብቆ ለስሜ ምስጋናና ክብር፣ የእኔ ሕዝብ እንዲሆንልኝ አድርጌው ነበር፤ ሕዝቤ ግን አልሰማም’ ይላል እግዚአብሔር።
ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ በርሱ ተጠብቆ ያለ ሥጋት ይረፍ፤ ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር የሚወድደውም ሰው በትከሻዎቹ መካከል ያርፋል።”
ሴቲቱም በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ መሄድ እንድትችል ሁለት የታላቁ ንስር ክንፎች ተሰጣት፤ ይህም የሆነው በዚያ ከእባቡ ፊት ርቃ ለአንድ ዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመን እኩሌታ በክብካቤ እንድትኖር ነው።
ጅራቱ የከዋክብትን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር ጣላቸው፤ እርሷም በወለደች ጊዜ ልጇን ለመዋጥ ፈልጎ ዘንዶው ልትወልድ በተቃረበችው ሴት ፊት ቆመ።