ዘዳግም 30:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ርግማን ሁሉ በሚጠሉህና በሚያሳድዱህ ጠላቶችህ ላይ ያደርገዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላክህም ይህን ርግማን ሁሉ በጠላቶችህና በሚጠሉህ በሚያሳድዱህም ላይ ያደርገዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህንም መርገሞች ሁሉ አንተን በሚጠሉህና በሚጨቊኑህ ጠላቶችህ ላይ ይመልስባቸዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህም እግዚአብሔር ይህችን መርገም ሁሉ በጠላቶችህና በሚጠሉህ በሚያሳድዱህም ላይ ያመጣታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህም እግዚአብሔር ይህችን መርገም ሁሉ በጠላቶችህና በሚጠሉህ በሚያሳድዱህም ላይ ያመጣታል። |
ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣ እንዲህ ይላል፤ “የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤
እነሆ፤ ስሜ የተጠራበትን ከተማ ማጥፋት እጀምራለሁ፤ ታዲያ ያለ ቅጣት ታመልጣላችሁን? ሳትቀጡ አትለቀቁም፤ በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ሳትቀጡ አታመልጡም፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’
“ ‘ነገር ግን አሟጥጠው የበሉህ ሁሉ እንደዚያው ይበላሉ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ለምርኮ ዐልፈው ይሰጣሉ፤ የሚዘርፉህ ይዘረፋሉ፤ የሚበዘብዙህም ሁሉ ይበዘበዛሉ።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ፍልስጥኤማውያን በቂም ተነሣሥተው በክፉ ልብ ተበቅለዋልና፣ ይሁዳንም በቈየ ጠላትነት ለማጥፋት ፈልገዋልና፤
ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፤ ‘የጌታ፣ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፣ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፣ የይሁዳም ቤት ተማርኮ በተወሰደ ጊዜ፣ “ዕሠይ!” ብላችኋልና፣
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ በልባችሁ ክፋት ሁሉ፣ በእስራኤል ውድቀት ላይ በመደሰት በእጃችሁ አጨብጭባችኋልና፤ በመዝለልም ጨፍራችኋልና
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ርኅራኄን በመንፈግ፣ ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፤ የቍጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣ መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የአሞን ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ድንበሩን ለማስፋት፣ የገለዓድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀድዷልና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የደማስቆ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ የብረት ጥርስ ባለው ማሄጃ፣ ገለዓድን አሂዳለችና፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጋዛ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ በመውሰድ፣ ለኤዶም ሸጣለችና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም። የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።
የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሷ ላይ በሚሰበሰቡበት በዚያ ቀን፣ ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ የማይነቃነቅ ዐለት አደርጋታለሁ፤ ለማነቃነቅ የሚሞክሩ ሁሉ ራሳቸውን ይጐዳሉ።
እንደ አንበሳ አድፍጠዋል፤ እንደ እንስቲቱም አንበሳ አድብተዋል፤ ሊቀሰቅሳቸውስ የሚችል ማን ነው? “የሚባርኩህ ቡሩክ፣ የሚረግሙህም ርጉም ይሁኑ።”
እግዚአብሔር ከማናቸውም በሽታ ነጻ ያደርግሃል፤ በግብጽ የምታውቃቸውን እነዚያን አሠቃቂ በሽታዎች በሚጠሉህ ሁሉ ላይ እንጂ በአንተ ላይ አያመጣብህም።