ዘዳግም 3:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እኛ በቤተ ፌጎር አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ቈየን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እኛም በቤተፌዖር ፊት ለፊት በሸለቆው ውስጥ ተቀመጥን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህም የተነሣ በቤትፔዖር ከተማ ፊት ለፊት ባለው ሸለቆ ውስጥ ቈየን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤተ ፌጎርም ፊት ለፊት በሸለቆው ውስጥ ተቀመጥን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤተፌጎርም ፊት ለፊት በሸለቆው ውስጥ ተቀመጥን። |
እግዚአብሔር በበኣል ፌጎር ላይ ምን እንዳደረገ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከመካከላችሁ በኣል ፌጎርን የተከተሉትን ሁሉ አጥፍቷቸዋል፤
ይህም ከግብጽ በወጡ ጊዜ በሙሴና በእስራኤላውያን ድል በተደረገው፣ በሐሴቦን በነገሠው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ በቤተ ፌጎር አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ነው።