ዘዳግም 28:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በጐተራህና እጅህ በነካው ሁሉ በረከቱን ይልካል። አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ላይ ይባርክሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ በጐተራህና እጅህ በነካው ሁሉ ላይ በረከቱን ይልካል። ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ላይ ይባርክሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ ጐተራህንና የእጅህን ሥራ ሁሉ ይባርክልሃል፤ እንዲሁም በሚሰጥህ ምድር ይባርክሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በረከቱን በአንተ ላይ፥ በጎተራህ፥ በእህልህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ይልካል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በረከቱ በአንተ ላይ በጎተራህ በእጅህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ያዝዛል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል። |
እርሱም በወራጅ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ነው፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
በጐተራ የቀረ ዘር አሁንም ይገኛልን? የወይኑና የበለሱ ዛፍ፣ የሮማኑና የወይራው ዛፍ እስካሁን አላፈሩም። “ ‘ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ።’ ”
ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ዐብረው ይደጉ። በዚያ ጊዜ ዐጫጆቹን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳትም እንዲቃጠል በየነዶው እሰሩት፤ ስንዴውን ግን ሰብስባችሁ በጐተራዬ ክተቱ እላቸዋለሁ’ አላቸው።”
እስኪ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
“እንዲህም አለ፤ ‘እንደዚህ አደርጋለሁ፤ ያሉኝን ጐተራዎች አፈርስና ሌሎች ሰፋ ያሉ ጐተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም ምርቴንና ንብረቴንም ሁሉ አከማቻለሁ፤
ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፣ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፣ አንተንም አምላክህ እግዚአብሔር በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።
በልግስና ስጠው፤ ስትሰጠውም ልብህ አይጸጸት፤ ከዚህም የተነሣ አምላክህ እግዚአብሔር በሥራህ ሁሉና እጅህ ባረፈበት በማናቸውም ነገር ይባርክሃል።
እርሱን በመተው ክፉ ድርጊት ከመፈጸምህ የተነሣ፣ እስክትደመሰስ ፈጥነህም እስክትጠፋ ድረስ እጅህ በነካው ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ርግማንን፣ መደናገርንና ተግሣጽን ይሰድድብሃል።
እግዚአብሔር በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ።