ዘዳግም 28:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጠላቶችህ በአንተ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ እግዚአብሔር እነርሱን ድል ያደርግልሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ይሸሻሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔርም ከእግርህ በታች ይወድቁ ዘንድ የሚቃወሙህን ጠላቶችህን በእጅህ ይጥላቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፤ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፥ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ። |
ኢዮሣፍጥ በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ ከቤርሳቤህ እስከ ኰረብታማው አገር እስከ ኤፍሬም ድረስ እንደ ገና በመውጣት ወደ ሕዝቡ መካከል ገብቶ ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ እግዚአብሔር መለሳቸው።
እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀቂያ ትሆናለህ።
መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው፣ እግዚአብሔር ካልተዋቸው በቀር፣ አንድ ሰው እንዴት ሺሑን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺሑን እንዲሸሹ ያደርጋሉ?
ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን ያሸነፈው በአንድ ዘመቻ ብቻ ነበር፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተዋግቶላቸዋልና።
ያደፈጡትም ሰዎች እንደዚሁ ከከተማዪቱ ወጥተው መጡባቸው። ስለዚህ እስራኤላውያን በዚያም በዚህም ስለ ከበቧቸው የጋይን ሰዎች ከመካከል አደረጓቸው፤ እስራኤላውያንም ሰዎቹን ፈጇቸው፤ አንድ እንኳ የተረፈ ወይም ያመለጠ አልነበረም፤