ዘዳግም 28:52 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትታመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከብባል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወርራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትተማመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪማረኩ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከባል፤ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር የሚገኙትን መኖሪያ ከተሞችህን ሁሉ ይከባሉ፤ አንተ የምትተማመንባቸውን ከፍተኞች የሆኑ ቅጽሮች ያሉአቸውን ምሽጎችህን ሁሉ ይደመስሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሀገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ፥ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ሁሉ ያጠፋሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ፥ በደጆች ሁሉ ያስጨንቅሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ደጆች ሁሉ ከብበው ያስጭንቁሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ በደጆች ሁሉ ከብበው ያስጨንቁሃል። |
እግዚአብሔር በቀኝ እጁ፣ በኀያል ክንዱም እንዲህ ሲል ምሏል፤ “ከእንግዲህ እህልሽን፣ ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤ ከእንግዲህ የደከምሽበትን፣ አዲስ የወይን ጠጅ ባዕዳን አይጠጡትም።
የያዕቆብን መኖሪያ ሁሉ፣ ጌታ ያለ ርኅራኄ ዋጣቸው፤ የይሁዳን ሴት ልጅ ምሽጎች፣ በቍጣው አፈረሳቸው፤ መንግሥቷንና መሳፍንቷን፣ በማዋረድ ወደ ምድር ጣላቸው።
ከስድሳ ሁለቱ ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፤ ምንም አይቀረውም። የሚመጣው አለቃ ሰዎችም፣ ከተማውንና ቤተ መቅደሱን ይደመስሳሉ። ፍጻሜውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ ጥፋትም ታውጇል።
ቃል ኪዳኔን ስላፈረሳችሁ፣ በላያችሁ ሰይፍ በማምጣት እበቀላችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ውስጥ በምትሰበሰቡበት ጊዜ ቸነፈር እሰድድባችኋለሁ፤ ለጠላትም እጅ ዐልፋችሁ ትሰጣላችሁ።
ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዪቱ ትያዛለች፤ ቤቶች ይበዘበዛሉ፤ ሴቶችም ይደፈራሉ፤ የከተማዪቱ እኩሌታ ይማረካል፤ የሚቀረው ሕዝብ ግን ከከተማዪቱ አይወሰድም።
እስክትጠፋም ድረስ የእንስሳትህን ግልገልና የምድርህን ሰብል ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅ ሆነ ዘይት፣ የመንጋህን ጥጃ ሆነ የበግና የፍየል መንጋህን ግልገል አያስቀርልህም።