ዘዳግም 27:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በዚያ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በዚያኑ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በዚያ ቀን እንዲህ ብሎ ሕዝቡን አዘዘ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በዚያን ቀን እንዲህ ብሎ ሕዝቡን አዘዘ፦ |
በዚያ ጊዜም ዳኞቻችሁን እንዲህ ስል አዘዝኋቸው፤ “በወንድሞቻችሁ መካከል የሚነሣውን ክርክር ያለ አድልዎ እዩት፤ ሙግቱ ወንድማማች በሆኑ እስራኤላውያን መካከል ወይም በአንድ እስራኤላዊና በመጻተኛ መካከል ቢሆን፣ በጽድቅ ፍረዱ።
እስራኤል በሙሉ መጻተኛውም ሆነ ተወላጁ፣ ሽማግሌዎቻቸውም ሆኑ ሹማምታቸው እንዲሁም ዳኞቻቸው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ተሸከሙት ሌዋውያን ካህናት ፊታቸውን አዙረው፣ በታቦቱ ግራና ቀኝ ቆመው ነበር። የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲባርኩ መመሪያ በሰጠ ጊዜ፣ አስቀድሞ ባዘዘው መሠረት፣ ግማሹ ሕዝብ በገሪዛን ተራራ፣ ግማሹ ደግሞ በጌባል ተራራ ፊት ለፊት ቆመ።