ዘዳግም 23:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእነርሱ የተወለዱላቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ መግባት ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም በሦስተኛው ትውልድ የሚወለዱ ልጆች ወደ ጌታ ጉባኤ ይግቡ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱም ከሦስተኛው ትውልድ በኋላ ዘሮቻቸው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባሎች ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በሦስተኛው ትውልድ የሚወለዱ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ቤት ይግቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም በሦስተኛው ትውልድ የሚወለዱ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ይግቡ። |
ከዚያም ወንድሙ ተወለደ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ወጣ፤ ከዚህም የተነሣ ስሙ ያዕቆብ ተባለ። ርብቃ ልጆቿን ስትወልድ፣ ይሥሐቅ የስድሳ ዓመት ሰው ነበር።
ሰሎሞን የግብጽ ንጉሥ የፈርዖን ወዳጅ ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ። እርሱም ቤተ መንግሥቱን፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የኢየሩሳሌምን ዙሪያ ቅጥር ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አስቀመጣት።
እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ መሪዎቹ ወደ እኔ መጥተው እንዲህ አሉኝ፤ “ካህናቱንና ሌዋውያኑን ጨምሮ የእስራኤል ሕዝብ ከጎረቤቶቻቸው ከከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኢያቡሳውያን፣ ከአሞናውያን፣ ከሞዓባውያን፣ ከግብጻውያንና ከአሞራውያን ርኩሰት ራሳቸውን አልለዩም።
ዐብሯችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደ ገዛ ወገናችሁ ይታይ፤ እንደ ራሳችሁም ውደዱት፤ እናንተም በግብጽ መጻተኞች ነበራችሁና፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።