ዘዳግም 23:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቈረጠ ማንኛውም ሰው ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የተኰላሸ ወይም ብልቱም የተሰለበ ሰው ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የተኰላሸ ወይም የተሰለበ ሰው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባል አይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ፍሬ ዘሩ የተቀጠቀጠ፥ አባለ ዘሩም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። |