La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 21:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሬሳው በተገኘበት አቅራቢያ ባለችው ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎች ሁሉ፣ በሸለቆው ውስጥ፣ ዐንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ሬሳው በተገኘበት አቅራቢያ ባለችው ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎች ሁሉ፥ በሸለቆው ውስጥ፥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ የተገደለው ሰው አስከሬን ወድቆ ለተገኘበት ስፍራ አቅራቢያ የሆነችው የዚያች ከተማ መሪዎች በጊደርዋ ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ተገ​ደ​ለው ሰው አቅ​ራ​ቢያ የሆ​ነ​ችው የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ቋን​ጃዋ በተ​ቈ​ረ​ጠው ጊደር ራስ ላይ እጃ​ቸ​ውን ይታ​ጠቡ፦

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ተገደለው ሰው አቅራቢያ የሆነችው የከተማይቱ ሽማግሌዎች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ አንገትዋ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ሲታጠቡ፦

Ver Capítulo



ዘዳግም 21:6
12 Referencias Cruzadas  

ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም አሠቃቂ የቈዳ በሽታ ያለበት፣ በምርኵዝ የሚሄድ ዐንካሳ፣ ወይም በሰይፍ ተመትቶ የሚወድቅ ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ ከኢዮአብ ቤት አይታጣ።”


ሰውነቴን በሳሙና ብታጠብ፣ እጄንም በልዩ መታጠቢያ ባነጻ፣


ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል? ከተሰወረ በደል አንጻኝ።


እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤


የድነቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤ አንደበቴም ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል።


በደሌን ፈጽሞ ዕጠብልኝ፤ ከኀጢአቴም አንጻኝ።


በሂሶጵ እርጨኝ፤ እኔም እነጻለሁ፤ ዕጠበኝ፤ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።


ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤ እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሯል!


በልዩ ቅጠል ብትታጠቢ፣ ብዙ ሳሙና ብትጠቀሚም፣ የበደልሽ ዕድፍ አሁንም በፊቴ ነው፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እንዲህም ብለው ይናገሩ፤ “እጆቻችን ደም አላፈሰሱም፤ ድርጊቱ ሲፈጸምም ዐይኖቻችን አላዩም።


እነዚህ ሁሉ እስከ መታደስ ዘመን ድረስ በምግብና በመጠጥ እንዲሁም የተለያዩ በመታጠብ የሚደረጉ የሥጋ ሥርዐቶች ብቻ ናቸው።