የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ሌዋውያኑ በምስጋና መዝሙር፣ በጸናጽል፣ በበገናና በመሰንቆ ድምፅ የምረቃውን በዓል በደስታ እንዲያከብሩ ከሚኖሩበት ተፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ዘዳግም 20:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለቆቹም ለሰራዊቱ እንዲህ ይበሉ፤ “አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ አለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አለቆቹም ለሠራዊቱ እንዲህ ይበሉ፤ ‘አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህ በኋላ የጦር መሪዎች ለዘማቾች እንዲህ ይበሉ፤ ‘አዲስ ቤት የሠራና አስመርቆ ያልገባበት ሰው በመካከላችሁ ይገኛልን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት ሌላ ሰው ቤቱን አስመርቆ ይገባበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሐፍትም ለሕዝቡ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ሰው ቢኖር በጦርነት እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያስመርቀው ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆችም ለሕዝቡ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ሰው ቢኖር በሰልፍ እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያስመረቀው ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። |
የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ሌዋውያኑ በምስጋና መዝሙር፣ በጸናጽል፣ በበገናና በመሰንቆ ድምፅ የምረቃውን በዓል በደስታ እንዲያከብሩ ከሚኖሩበት ተፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ስለዚህ እኔም የየነገዶቻችሁን አለቆች ጥበበኞችንና የተከበሩትን ሰዎች ተቀብዬ፣ ሻለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች እንዲሁም የየነገዱ ሹማምት በማድረግ በእናንተ ላይ ሥልጣን እንዲኖራቸው ሾምኋቸው።
ይህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፍ ለክፍል አዛዣቸው ዐብረህ ውሰድ፤ ወንድሞችህም እንዴት እንደ ሆኑ አይተህ፣ ደኅንነታቸውን የሚያረጋግጥ ምልክት ከእነርሱ ዘንድ አምጣልኝ።