ስለዚህ በአገርህ እንድናልፍ እባክህን ፍቀድልን፤ በየትኛውም ዕርሻ ወይም የወይን ተክል ውስጥ አንገባም፤ ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። የንጉሡን አውራ ጐዳና ይዘን ከመጓዝ በቀር፣ ግዛትህን ዐልፈን እስክንሄድ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”
ዘዳግም 2:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምንበላውን ምግብ፣ የምንጠጣውንም ውሃ በጥሬ ብር ሽጥልን። በእግር እንድናልፍ ብቻ ፍቀድልን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፤ የምጠጣውንም ውሃ በገንዘብ ስጠኝ፤ በእግሬ እንዳልፍ ብቻ ፍድልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለምንበላው ምግብና ለምንጠጣው ውሃ ዋጋ እንከፍላለን፤ እኛ የምንፈልገው በአንተ አገር በኩል ማለፍ እንዲፈቀድልን ብቻ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፤ የምጠጣውንም ውኃ በገንዘብ ስጠኝ፤ በእግሬ ብቻ ልለፍ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፥ የምጠጣውንም ውሓ በገንዘብ ስጠኝ፤ በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች በዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ ብቻ በእግሬ ልለፍ። |
ስለዚህ በአገርህ እንድናልፍ እባክህን ፍቀድልን፤ በየትኛውም ዕርሻ ወይም የወይን ተክል ውስጥ አንገባም፤ ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። የንጉሡን አውራ ጐዳና ይዘን ከመጓዝ በቀር፣ ግዛትህን ዐልፈን እስክንሄድ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”
እስራኤላውያንም መልሰው፣ “አውራውን መንገድ ይዘን እንሄዳለን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን የትኛውንም ውሃችሁን ከጠጣን ዋጋውን እንከፍላለን፤ በእግር ዐልፈን መሄድ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አንፈልግም።” አሏቸው።