ከዚህም በቀር ኢዮስያስ ሙታን አነጋጋሪዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን፣ የየቤተ ሰቡ ሰውን አማልክት፣ ጣዖታትን እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የተገኙትን ሌሎች አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ አስወገደ፤ ይህን ያደረገውም ካህኑ ኬልቅያስ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈው የሕጉ ቃል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው።
ዘዳግም 18:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነውና። ከእነዚህ አስጸያፊ ልምዶች የተነሣም አምላክህ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነውና፥ ከእነዚህ አጸያፊ ልምዶች የተነሣም ጌታ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላና አጸያፊ ነው፤ አንተ ወደ ፊት በተራመድህ ቊጥር አምላክህ እግዚአብሔር አሕዛብን ከፊትህ ነቃቅሎ የሚያሳድድበት ምክንያት ይህንኑ ዐይነት የረከሰ ሥራ በማድረጋቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያጠፋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው፤ ስለዚህም ርኩሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል። |
ከዚህም በቀር ኢዮስያስ ሙታን አነጋጋሪዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን፣ የየቤተ ሰቡ ሰውን አማልክት፣ ጣዖታትን እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የተገኙትን ሌሎች አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ አስወገደ፤ ይህን ያደረገውም ካህኑ ኬልቅያስ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈው የሕጉ ቃል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው።
አምላክህ እግዚአብሔር እነርሱን ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ በልብህ፣ “ይህችን ምድር እንድወርስ እግዚአብሔር ወደዚህ ያመጣኝ፣ ከጽድቄ የተነሣ ነው” አትበል። በዚህ አይደለም፤ እነዚህን አሕዛብ እግዚአብሔር ከፊትህ የሚያሳድዳቸው በክፋታቸው ምክንያት ነው።
ምድራቸውን ገብተህ የምትወርሳት ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሣ ሳይሆን፣ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም አምላክህ እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ከክፋታቸው የተነሣ ከፊትህ ስለሚያባርራቸው ነው።