ዘዳግም 12:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ደማቸውን አትብላ፤ ደሙን እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ አፍስሱት እንጂ አትብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። |
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ዐይኖቻችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምም ታፈስሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ታስባላችሁ?
ለጣዖት ከተሠዋ ነገር፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከዝሙት ርኩሰት እንድትርቁ ነው። ከእነዚህ ዐይነት ነገሮች ብትርቁ ለእናንተ መልካም ነው። ደኅና ሁኑ።
ከዚያም ለሳኦል፣ “እነሆ፤ ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት እግዚአብሔርን እየበደለ ነው” ተብሎ ተነገረው። ሳኦልም፣ “ሕግ ተላልፋችኋል፤ በሉ አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ አቅርቡልኝ” አለ።