አሞጽ 9:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ እስራኤላውያን፣ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር “እስራኤልን ከግብጽ፣ ፍልስጥኤማውያንን ከቀፍቶር፣ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?” ይላል ጌታ። “እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእኔ ዘንድ ኢትዮጵያውያን ከእናንተ አያንሱም፤ እናንተን ከግብጽ እንዳወጣሁ እንደዚሁም ፍልስጥኤማውያንን ከቀርጤስ፥ ሶርያውያንን ከቂር አላወጣሁምን? አውጥቻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብፅ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከቀጰዶቅያ፥ ሶርያውያንንም ከጕድጓድ ያወጣሁ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን? |
እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብጻውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብጽን ያዋርዳል።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ።
ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣ ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣ ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣ ቀኑ ደርሷልና። እግዚአብሔር በቀፍቶር ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋ ተነሥቷል።
የደማስቆን በሮች እሰባብራለሁ፤ በቤት ዔደን በትር የያዘውን፣ በአዌን ሸለቆ ያለውን ንጉሥ እደመስሳለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል” ይላል እግዚአብሔር።
እስከ ጋዛ ድረስ ባሉት መንደሮች የኖሩትን ኤዋውያን በተመለከተም፣ ከቀፍቶር ወጥተው የመጡት ከቀፍቶሪማውያን፣ እነርሱን አጥፍተው መኖሪያቸውን እዚያው አደረጉ።