ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ አናግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል።
ሐዋርያት ሥራ 7:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሁለተኛ ጊዜ ሲሄዱ ደግሞ ዮሴፍ ማንነቱን ለወንድሞቹ ገለጠ፤ ፈርዖንም ስለ ዮሴፍ ዘመዶች ተረዳ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለተኛውም ዮሴፍ ለወንድሞቹ ታወቀ፤ የዮሴፍም ትውልድ በፈርዖን ዘንድ ተገለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳግመኛ ወደ ግብጽ ተመልሰው በሄዱ ጊዜ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ተገለጠ፤ ቤተ ዘመዱም በፈርዖን ዘንድ ታወቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ግብፅም እንደ ገና በተመለሱ ጊዜ ወንድሞቹ ዮሴፍን ዐወቁት፤ ፈርዖንም የዮሴፍን ዘመዶች ዐወቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለተኛውም ዮሴፍ ለወንድሞቹ ታወቀ፥ የዮሴፍም ትውልድ በፈርዖን ዘንድ ተገለጠ። |
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ አናግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል።