ሐዋርያት ሥራ 7:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ጊዜም በግብጽና በከነዓን አገር ሁሉ ታላቅ መከራን ያስከተለ ራብ መጣ፤ አባቶቻችንም የሚበሉትን ዐጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፤ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በግብጽና በከነዓን አገር ሁሉ ላይ ታላቅ ችግር ያስከተለ ራብ ሆነ፤ አባቶቻችንም ምግብ ሊያገኙ አልቻሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፅና በከነዓን ሀገር ሁሉ ረኃብና ታላቅ ጭንቅ መጣ፤ አባቶቻችንም የሚበሉት አጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብፅና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፥ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም። |
ገና ወደ ፊት የሚመጣ የዐምስት ዓመት ራብ ስላለ፣ በዚያ የሚያስፈልጋችሁን እኔ እሰጣችኋለሁ፤ አለዚያ ግን አንተና ቤተ ሰዎችህ ያንተም የሆነው ሁሉ፣ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።’
ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት።