ሐዋርያት ሥራ 12:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ አስገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ አስገደለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። |
እርሱም፣ “እኔ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ እስራኤላውያን ኪዳንህን ትተዋል፤ መሠዊያዎችህን አፍርሰዋል፤ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና። የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አሁንም እኔን ለመግደል ይፈልጋሉ” አለ።
እነርሱም ኦርዮን ከግብጽ አምጥተው፣ ወደ ንጉሥ ኢዮአቄም ወሰዱት፤ እርሱም በሰይፍ ገደለው፤ ሬሳውንም ተራ ሰዎች በሚቀበሩበት ስፍራ ጣለው።
እርሱም፣ “ከጽዋዬ በርግጥ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን በቀኜና በግራዬ መቀመጥ አባቴ ላዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምፈቅደው ነገር አይደለም” አላቸው።
በድንጋይ ተወገሩ፤ በመጋዝ ለሁለት ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተወግተው ሞቱ፤ እየተጐሳቈሉ፣ እየተሰደዱና እየተንገላቱ የበግና የፍየል ቈዳ ለብሰው ዞሩ፤